You Versus the Internet
የግላዊነት ፖሊሲ
ዲጂታል ፐብሊክ ስኩዌር (“ዲፒኤስ”፣ “እኛ” ወይም “የእኛ”) በhttp://eth.versustheinternet.com/ (አንድላይ “ሳይቱ” ተብለው የሚጠሩ) የሚገኙትን የእኛን ዌብሳይቶች የሚጎብኙትን ሰዎችን ግላዊነት ለመጠበቅ ቁርጠኛ ነው። ሳይቱ ሁሉንም ዳውንሎድ መደረግ የሚችሉ አፕሊኬሽኖች፣ ፊቸሮች፣ አሠራሮች (ፈንክሽናሊቲዎች) ፣ ይዘቶች (ኮንቴንቶች)፣ ወይም በሳይቱ ሊገኙ የሚችሉ ወይም በሳይቱ የቀረቡ መረጃዎችን እና ሌሎች ማንኛቸውም የሚዲያ አይነት፣ የሚዲያ ቻናል፣ የሞባይል ድረ ገጽ፣ ወይም የሞባይል አፕሊኬሽን እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ የተዛመዱ ወይም የተገናኙ እስከሆኑ ድረስ ያካትታሉ። የተጠቃሚዎቻችንን ግላዊነት እናከብራለን፤ እናም ተልዕኮአችንን ለማስቀጠል ግላዊ የሆኑ መረጃዎችን ከእርስዎ ከመውሰዳችን በፊት ማንኛውንም አስፈላጊ መረጃ ልናቀርብልዎ እንተጋለን። ይህ የግላዊነት ፖሊሲ የሚተገበርባቸው ሁኔታዎችን በተመለከተ ኃላፊነት የሚወስደው አካል እኛ ነን፤ እርስዎ ሳይቱን ሲጠቀሙ ለሚሰጡት ግላዊ መረጃ ኃላፊነት የምንወስደው እኛ ነን።
ይህ የግላዊነት ፖሊሲ የአጠቃቀም መመሪያዎች አንዱ አካል ነው፤ እርስዎ ሳይታችንን በሚጎበኙ ጊዜ እኛ የእርስዎን ግላዊ መረጃ እንዴት እንደምንሰበስብ፣ እንደምንጠቀም፣ አሳልፈን እንደምንሰጥ፣ እና እንደምንጠብቅ ያስረዳል። ሳይቱ ለእርስዎ የቀረበው ለትምህርት እና ምርምር እንዲጠቀሙበት ነው።
በሳይቱ አማካይነት በፍቃደኝነት ግላዊ መረጃዎችን ለእኛ በመስጠትዎ፣ ተገቢ በሆነበት ቦታ ሁሉ፣ እንዲሰበሰብ፣ እንድንጠቀመው፣ አሳልፈን እንድንሰጠው በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ እየተስማሙ ነው። ይህን መሰል ግላዊ መረጃ ከአሁኑ መገኛዎ ወደ ዲፒኤስ ጽሕፈት ቤቶች እና ሰርቨሮች፣ እንዲሁም በካናዳ እና በዩናይትድ ስቴትስ ወደሚገኙ ሥልጣን የተሰጣቸው ሦስተኛ ወገኖች ሊዘዋወር እንደሚችል ዕውቅና እየሰጡ እና እየተስማሙ ነው።
እባክዎ ይህን የግላዊነት ፖሊሲ በጥንቃቄን ያንብቡ። በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ መመሪያዎች ካልተስማሙ እባክዎ ሳይቱን አይጠቀሙ። በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ላይ በማንኛውም ጊዜ እና በማንኛውም ምክንያት ለውጦችን የማድረግ መብታችን የተጠብቀ ነው። ማንኛቸውም ለውጦች ሲኖሩ የዚህን የግላዊነት ፖሊሲ “መጨረሻ የዘመነው” የሚለውን ቀን በማዘመን እናሳውቅዎታለን። ማንኛቸውም አይነት ለውጦች እና ቅያሪዎች የዘመነው የግላዊነት ፖሊሲ ሳይቱ ላይ ከሚለጠፍበት ቅጽበት አንስቶ ተፈጻሚ ይሆናሉ። ስለ አዳዲስ ለውጦች ለመከታተል በየጊዜው የግላዊነት ፖሊሲውን ቢመለከቱ ጥሩ ነው። ለውጥ የተደረገበት የግላዊነት ፖሊሲ ከተለጠፈበት ቀን በኋላ ሳይቱን መጠቀም ከቀጠሉ ስለ ለውጦቹ እንዳወቁ፣ ለውጦቹን እንደተቀበሉ፣ እና ለውጦቹ እርስዎም ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆኑ ይቆጠራል።
በዚህ መድረክ ላይ የሚኖርዎት ተሳትፎ በፈቃደኝነትዎ ላይ የተመሠረተ ነው ፤ ከሳይቱ በማንኛውም ጊዜ መውጣት ይችላሉ።
የመረጃዎ መሰብሰብ
ግላዊ መረጃ ማለት እርስዎን እንደ ግለሰብ (ወይም እንደ ሕጋዊ ግለሰብ፣ ተገቢ በሆነበት ቦታ) ለመለየት የሚያስችል መረጃ ነው። እኛ የምንሰበስበው ወይም የምናገኘው መረጃ የሚከተሉትን ያካትታል፦
- እኛን በኢሜይል በማግኘት ለእኛ የሚሰጡን መረጃ። ስምዎን፣ አድራሻዎን፣ ስልክ ቁጥርዎን፣ ኢሜይል አድራሻዎን ወይም መሰል ግላዊ መረጃዎችን በሳይቱ አማካይነት አንሰበስብም።
- አጠቃላይ የአጠቃቀም ዳታ፡ እርስዎ ሳይቱን ሲጎበኙ ሰርቨሮቻችን አውቶማቲካሊ የሚሰበስቧቸው መረጃዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦ የብራውዘርዎን አይነት፣ ኦፕሬቲንግ ሲስተምዎ፣ የተጠቀሙበት ሰዓት፣ እና በሳይታችን ላይ የጎበኟቸው ገጾች። የኢንተርኔት ፕሮቶኮል (አይፒ) አድራሻዎን በሰርቨሮቻችን ላይ አንመዘግብም። አይፒ አድራሻዎች ለደኅንነት ሲባል በደኅንነት አቅራቢያችን ተቀማጭ ሊደረጉ ይችላሉ። እርስዎ ሳይታችንን እየተጠቀሙ ከሆነ ይህ መረጃ የመሣሪያዎን (ዲቫይስዎን) አይነት፣ የዲቫይስዎን የሲስተም ቋንቋ፣ እና የከተማ መገኛ፣ የኦፕሬቲንግ ሲስተምዎን፣ አገርዎን፣ እና ሌሎች ከሳይቱ ጋር የሚያድርጓቸውን ምልልሶች ሊያካትት ይችላል።
- ኩኪዎች፡ በተጨማሪም ሳይታችንን ሲጎበኙ እርስዎ በሳይታችን ስለሚኖርዎት እንቅስቃሴ አንዳንድ መረጃዎችን እንሰበስባለን፣ ይህ ከታች በበለጠ ተብራርቷል።
ሳይቱ የሚተዳደረው ካናዳ ውስጥ በእኛ ነው፤ ነገር ግን በሳይታችን አማካይነት የሚሰበሰቡ ማንኛቸውም መረጃዎችን በካናዳ ውስጥ ወይም በዩናይትድ ስቴትስ ልናዘዋውር፣ ፕሮሰስ ልናደርግ፣ ወይም ልናከማች እንችላለን። እባክዎ ይህ በእርስዎ አገር የሚያገኙትን ያህል ከለላ ላይሰጥዎ እንደሚችል ያስተውሉ።
ኩኪዎች እና የዌብ አናሊቲክስ
እኛ ጉግል አናሊቲክስን እንተቀማለን፤ እሱም እኛ መሠረታዊ የጌም ፈንክሽናሊቲዎችን እና የተጠቃሚዎቹ ማንነት ሳይገለጥ የአጠቃቀም ስታቲስቲኮችን ለመከታተል እንዲረዳን አንድ ኩኪ ይከትታል። “ኩኪ” ማለት የእኛ ሳይት ለእርስዎ ብራውዘር ሊልከው የሚችለው ትንሽ የዳታ ቋት ነው፣ ይህ ደግሞ በዲቫይስዎ ላይ ተቀማጭ ሊደረግ ይችላል። ስለ ግላዊነትዎ እና ስለ የኩኪ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስጋት ከገባዎ ኩኪ ሲደርስዎ ብራውዘርዎ እንዲያሳውቅዎ ማድረግ ይችላሉ። ሳይታችን ሊልክልዎ የሚሞክራቸውን ኩኪዎች ብራውዘርዎ ጨርሶ እንዳይቀበል ማድረግም ይችላሉ። ነገር ግን ኩኪዎችን ለማጥፋት ወይም ለመከልከል ከወሰኑ እባክዎ ሳይታችን በተገቢው ሁኔታ ላይሰራልዎ እንደሚችል ያስተውሉ።
ዲፒኤስ የጉግል አናሊቲክስ መዝገቦችን ማየት አይችልም፣ እነዚህ የእርስዎን ስም አይይዙም፣ ነገር ግን ከእርስዎ ጋር በቅርበት የሚቆራኙ መረጃዎን ይይዛሉ። የእርስዎን ማንነት ሊገልጡ የሚችሉ መረጃዎችን ተቀማጭ ከማድረግ ለመቆጠብ በሳይታችን ላይ አይፒ አድራሻዎችን መደበቂያ እና የጉግል አናሊቲክስ መደበቂያ አሠራሮ እንጠቀማለን። ስለ ጉብኝትዎ የምመዘግባቸው መረጃዎች የእርስዎን ማንነት ሊገልጡ የማይችሉትን ብቻ (ለምሳሌ፦ ምን ላይ ክሊክ ተደረገ፣ የሰርቬይ መልሶች፣ እና ሌሎች ስብስብ ዳታዎች) ሲሆኑ እነዚህን የምንጠቀመውም የተጠቃሚዎችን የሳይቱ አጠቃቀሞችን አናላይዝ ለማድረግ እና ለመከታተል፣ የትኞቹ ኮንቴንቶች ተወዳጅ ናቸው የሚለውን ለማወቅ፣ እና የኦንላይን አክቲቪቲዎችን በተሻለ ለመረዳት ነው።
የመረጃዎ ጥቅም ላይ መዋል እና ተላልፎ መሰጠት
ስብስብ፣ ማንነትን የሚገልጡ መረጃዎች የተሰረዙባቸው ስታቲስቲካዊ ዳታዎችን እና አናሊሲሶችን ራሳችን ለመጠቀም፣ ለሕዝብ ለማጋራት፣ እና የፕሮጀክት ፕሮግረስ ሪፖርት ለማድረግ እንጠቀምበታለን። በተጨማሪም ግላዊ መረጃዎን በሌሎች መንገዶች እርስዎ ከተስማሙ ወይም ገዢው ሕግ በሚፈቅድባቸው መንገዶች እንጠቀማለን። ሳይቱን በመጠቀም እኛ ማንነትን የሚገልጡ መረጃዎች የተሰረዙባቸው ወይም በሌላ ሐሰተኛ ስም የተቀየሩባቸው መረጃዎችን ለመሰብሰብ፣ ለመጠቀም፣ ለማጋራት፣ እና ለማከማቸት ሥልጣን እንዳለን እርስዎ ይስማማሉ። እነዚህም መረጃዎች ለቤንችማርኪንግ፣ ለአናሊቲክስ፣ ለሜትሪክስ፣ ለሪሰርች፣ ለሪፖርቲንግ፣ ለማሽን ለርኒንግ፣ እና ለሌሎች የቢዝነስ ዓላማዎች እንዲውሉ በሳይቱ በኩል የሚሰበሰቡ ናቸው።
በሕግ ከተገደድን ወይም ድርጊቱ የሕግ አሠራሮችን ለመከተል፣ ለክሶች መልስ ለመስጠት፣ ወይም የዲፒኤስን፣ የአጋሮቹን፣ የተጠቃሚዎቹን፣ የአገልግሎት አቅራቢዎቹን፣ ወይም የሕዝቡን መብቶች፣ ንብረቶች ወይም ደኅነንትን ለመጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነ ካመንን ግላዊ መረጃን አሳልፎ የመስጠት መብታችን የተጠበቀ ይሆናል።
ግላዊ መረጃዎችን ለአጋሮቻችን ወይም ለሌሎች ማንኛቸውም የቢዝነስ ሽርኮቻችን ወይም ለእንደራሴ ኤጀንቶች ወይም ለፋይናንስ፣ ለኢንሹራንስ፣ ለሕግ፣ ለአካውንቲንግ፣ ወይም መሰል ፕሮፌሽናል አገልግሎቶችን ለሚያቀርቡልን አማካሪዎቻችን ልናጋራ እንችላለን።
ግላዊ መረጃዎ እንደ እኛ ሆኖ እንደ ዳታ ፕሮሰሲንግ፣ ወይም ዶኩመንት ሪቴንሽን የመሳሰሉ ሥራዎችን እንዲሠራ በእኛ ለተቀጠረ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተላልፎ ሊሰጥ ይችላል። ይህን መሰል የግላዊ መረጃዎ ተላልፎ መሰጠት የሚከናወነው ፍጹም ምስጢራዊነቱ በተጠበቀ መንገድ ነው፣ መረጃው ጥቅም ላይ የሚውለውም ለተጋራበት ዓላማ ብቻ ይሆናል። ድርጅቱ ወይም ግለሰቡ ይህን ግላዊነት ፖሊሲ መጠበቁን እናረጋግጣለን።
ተፈጻሚ የሚሆኑ መመሪያዎች ላይ ተመሥርተን ግላዊ መረጃዎን ለመንግሥት ኤጀንሲ፣ ለፍርድ ቤት፣ ወይም ለሕግ ማስከበር አካላት አሳልፈን ልንሰጥ እንችላለን።
የመረጃዎ ደኅነነት
ግላዊ መረጃዎን ለመጠበቅ እንዲረዳን ተገቢዎቹን የአስተዳደር፣ የቴክኒክ፣ እና ኦርጋናይዜሽን እና የፊዚካል ደኅንነት ርምጃዎችን እንወስዳለን። እርስዎ የሚያቀርቡልንን ግላዊ መረጃ ደኅነንት ለማስጠበቅ ተገቢዎቹን ርምጃዎች የወሰድን ቢሆንም፣ እባክዎ ማንኛቸውም ርምጃዎች ፍጹም እና የማይሰበሩ ሊሆኑ እንደማይችሉ፣ እንዲሁም ማንኛውም አይነት የዳታ ዝውውር ከመጠለፍ ወይም አለአግባብ ጥቅም ላይ ከመዋል ዋስትና ሊኖረው እንደማይችል ያስታውሱ። ማንኛውም ኦንላይን የሚሰጥ መረጃ ሥልጣን ባልተሰጣቸው አካላት ለጠለፋ እና ለሌላ አለአግባብ ጥቅም ላይ ለመዋል ተጋላጭ ነው። ስለዚህ ግላዊ መረጃን እርስዎ ሲሰጡ እኛ ፍጹም የሆነ ደኅንነትን ልናረጋግጥ አንችልም።
የአትከታተል ፊቸሮች መቆጣጠሪያዎች
አብዛኛዎቹ የዌብ ብራውዘሮች እና አንዳንድ የሞባይል ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች የአትከታተል (ዱ ኖት ትራክ “ዲኤንቲ”) ፊቸር ወይም ሴቲንግ አላቸው። ይህን በማብራት የግላዊነት ምርጫዎን መጠቆም እና ኦንላይን የሚያደጓቸው የብራውዚንግ አክቲቪቲዎች እንዳይመዘገቡ እና ተቀማጭ እንዳይደረጉ ማድረግ ይችላሉ። ከእኛ ልምድ፣ ብዙ ሰዎች ስለ ዲኤንቲ ዕውቀቱ የላቸውም፣ የብራውዘር ሴቲንጋቸውንም እንደዚህ አላደረጉም። እንደ ዩኒቨርሳል ፖሊሲ አፕሮች፣ በሳይታችን ላይ ለዲኤንቲ የብራውዘር ሲግናሎች ወይም ለሌሎች የእርስዎን የአትከታተሉኝ ምርጫ የሚያሳውቁ አሠራሮች መልስ አንሰጥም፤ በፈንታው በሳይቱ ላይ የሚሰበሰቡ ዳታዎችን ሁሉ ማንነትን የሚገልጡ መረጃዎች እንሰርዛለን (አኖኒማይዝ እናደርጋለን)፣ ይህም ሁሉም ሰው ግላዊነቱን እንዲጠብቅ ለማድረግ መቻሉን ለማረጋገጥ ነው።
በሦስተኛ ወገን ዌብሳይቶች ጥቅም ላይ የሚውሉ ግላዊ መረጃዎች
አልፎ አልፎ እኛ ወደማንቆጣጠራቸው ወይም ወደማንንከባከባቸው ዌብሳይቶች የሚወስዱ ሊንኮችን እናካትታለን። እርስዎ ለሦስተኛ ወገን ዌብሳይቶች ለሚሰጡት ግላዊ መረጃ ወይም በሦስተኛ ወገን ዌብሳይቶች ለሚሰበሰቡ ግላዊ መረጃዎች ኃላፊነት አንወስድም። እርስዎ ጥያቄዎች ካለዎ ወይም ያሳሰበዎ ነገር ካለ የሦስተኛ ወገን ዌብሳይቶችን የግላዊነት ፖሊሲዎች ይመርምሩ ወይም የሦስተኛ ወገን ዌብሳይቱን ኦፕሬተር ያግኙ።
የዕድሜ ገደብ
ሳይቱ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎችን ለማገልገል ወይም ለመሳብ ዲዛይን የተደረገ አይደለም። ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ከሆኑ ሰዎች እያወቅን ግላዊ መረጃዎችን አንሰበስብም። ከ18 ዓመት በታች የሆነ ማንኛውም ሰው ሳይቱን መጠቀም የለበትም።
የእርስዎ መረጃ ማግኘት እና መቆጣጠር
በማንኛውም ጊዜ እኛ ወደፊት እርስዎን ኮንታክት እንዳናደርግዎ ማድረግ ይችላሉ። እኛን በሳይታችን በተቀመጠው ኢሜይል አድራሻ ወይም ስልክ ቁጥር ኮንታክት በማድረግ የሚከተለውን በማንኛውም ጊዜ ማድረግ ይችላሉ፦ እኛ ስለ እርስዎ ምን አይነት ዳታ እንዳለን ማየት፣ ላይኖረን ይችላል፤ እኛ ስለ እርስዎ ያለንን ማንኛውም ዳታ መቀየር/ማረም፤ እኛ ስለ እርስዎ ያለን ማንኛውም ዳታ እንዲሰረዝ መጠየቅ፤ እኛ የእርስዎን ዳታ ስለምንጠቀምበት መንገድ ያሳሰበዎትን ነገር መግለጽ።
የዲፒኤስ የቢዝነስ ቦታ የሚገኘው ቶሮንቶ፣ ኦንታሪዎ፣ ካናዳ ነው። ግላዊ መረጃዎን ወይም ይህን የግላዊነት ፖሊሲን በሚመለከት ማንኛቸውም አይነት መጠይቆች፣ ጥያቄዎች ወይም አስተያየቶች ካሉዎ በኢሜይል privacy@digitalpublicsquare.org ላይ ኮንታክት ሊያደርጉን ይችላሉ።