የአገልግሎት መመሪያዎች

እነዚህ ዌብሳይት በhttp://eth.versustheinternet.com/ የሚገኙ (አንድ ላይ “ሳይቱ” የሚባሉ) ኦፕሬት የሚደረጉት በዲጂታል ፐብሊክ ስኩዌር (“ዲፒኤስ”፣ “እኛ” ወይም “የእኛ”) ሲሆን የተሠሩትም በኢትዮጵያ ለሚገኙ ተጠቃሚዎች ነው። ሳይቱ ሁሉንም ዳውንሎድ መደረግ የሚችሉ አፕሊኬሽኖች፣ ፊቸሮች፣ አሠራሮች (ፈንክሽናሊቲዎች) ፣ ይዘቶች (ኮንቴንቶች)፣ ወይም በሳይቱ ሊገኙ የሚችሉ ወይም በሳይቱ የቀረቡ መረጃዎችን እና ሌሎች ማንኛቸውም የሚዲያ አይነት፣ የሚዲያ ቻናል፣ የሞባይል ድረ ገጽ፣ ወይም የሞባይል አፕሊኬሽን እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ የተዛመዱ ወይም የተገናኙ እስከሆኑ ድረስ ያካትታሉ።

ሳይቱ ለእርስዎ የቀረበልዎ ለትምህርት እና ምርምር ዓላማዎች እንዲጠቀሙበት ነው።

እነዚህ የአገልግሎት መመሪያዎች (“መመሪያዎች”) እርስዎ ይህን ሳይት ሲያገኙ እና ሲጠቀሙ እርስዎ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑትን መመሪያዎች እና ሁኔታዎች ያስቀምጣሉ። የእርስዎ አገልግሎቶቹን መጠቀም ላይ የግላዊነት ፖሊሲያችን (“ግላዊነት ፖሊሲ”) መመሪያዎች ተፈጻሚ እንደሚሆኑ ይስማማሉ። ይህ ግላዊነት ፖሊሲም በሬፈረንስ ከአገልግሎት መመሪያዎቹ ጋር የተካተተ እና የአገልግሎት መመሪያዎቹ ዋነኛ ነጥቦች ውስጥ አንዱ ነው።

ሳይቱን በመጠቀምዎ የእነዚህን የአገልግሎት መመሪያዎች ደንቦች እና ሁኔታዎች እንዳነበቡ ይቆጠራል፣ ብሎም እርስዎ ሳይቱን የሚከፍቱበትን እና የሚጠቀሙበትን አሠራር የሚያስተዳድሩት እነዚህ ደንቦች የሚያስቀምጧቸውን እነዚህን መመሪያዎች እርስዎ እንደተቀበሉ እና በእነዚህ ለመገዛት መፍቀድዎን እየጠቆሙ ነው። ከእነዚህ መመሪያዎች ውስጥ በአንዱም ይሁን በብዙው ካልተስማሙ ሳይቱን መክፈትም ሆነ መጠቀም አይችሉም፤ ከሳይቱ መውጣትም ይኖርብዎታል። እነዚህ መመሪያዎች እርስዎ ሳይቱን በመጠቀምዎ ለሚመጡ ጉዳቶች እኛ ላይ ከሚደርሱብን የካሣ ክሶች እርስዎ የሚለቅቁበትን መልቀቂያ አካትተዋል። ሳይቱን በመጠቀምዎ እነዚህን ቅድመ መመሪያዎች መቀበልዎን ያረጋግጣሉ።

በእነዚህ መመሪያዎች በመስማማትዎ ዕድሜዎ ቢያንስ 18 ዓመት መሆኑን እና የኢትዮጵያ ነዋሪ መሆንዎን ይወክላሉ።

ማዘመኛዎች (አፕዴቶች)

በማንኛውም ጊዜ እና ለማንኛውም ምክንያት በእነዚህ መመሪያዎች ላይ ለውጥ የማድረግ መብታችን የተጠበቀ ነው። ማንኛቸውም ለውጦች ሲኖሩ የእነዚህን መመሪያዎች “መጨረሻ የዘመነው” የሚለውን ቀን በማዘመን እናሳውቅዎታለን። ማንኛቸውም አይነት ለውጦች እና ቅያሪዎች የዘመኑት መመሪያዎች ሳይቱ ላይ ከሚለጠፉበት ቅጽበት አንስቶ ተፈጻሚ ይሆናሉ። ስለ አዳዲስ ለውጦች ለመከታተል በየጊዜው የግላዊነት ፖሊሲውን ቢመለከቱ ጥሩ ነው። ለውጥ የተደረገባቸው መመሪያዎች ከተለጠፉበት ቀን በኋላ ሳይቱን መጠቀም ከቀጠሉ ስለ ለውጦቹ እንዳወቁ፣ ለውጦቹን እንደተቀበሉ፣ እና ለውጦቹ እርስዎም ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆኑ ይቆጠራል።

የመመርመሪያ አገልግሎት አይደለም

ሳይቶቹ የመማሪያ መሣሪያዎች ናቸው፤ ለሚከተሉት መሰል ዓላማዎች የተሠሩ አይደሉም፦ እንደ የመመርመሪያ አገልግሎት፤ እንደ በምርመራ ወቅት ማረጋገጫ መስጫ አገልግሎት፤ የሕመሞችን ሕክምና መምረጫ፣ መምሪያ፣ ወይም አገልግሎት ማበረታቻ፤ በአደገኛ ወይም ሚሽን-ክሪቲካል (እጅግ አስፈላጊ) ሁኔታዎች ውስጥ ጥቅም ላይ ለማዋል ወይም ስሕተት አልባ አሠራር በሚጠይቁ ጊዜዎች ለመጠቀም፤ ወይም ስሕተት ለሞት ወይም ለግለሰባዊ (አካላዊ) ጉዳት ሊያጋልጥ በሚችልባቸው ሁኔታዎች (በአጠቃላይ “ያልተፈቀዱ ዓላማዎች”)። ሳይቶቹ ለእንደ እነዚህ አይነት ያልተፈቀዱ ዓላማዎች ያልተሠራ፣ ያልታሰበ፣ እና ያልተፈቀደ እንደመሆኑ መጠን ሳይቱንም ሆነ ማንኛውንም እዚያ የሚቀርብ መረጃን ላልተፈቀዱ ዓላማዎች ወይም ለሌሎች መሰል ዓላማዎች መጠቀም አይችሉም።

በዚህ ሳይት ላይ የሚገኝ የሕክምናም ሆነ ሌላ አይነት መረጃ ትክክለኛ፣ የተሟላ፣ ወይም ወቅታዊ ካልሆነ እኛ ኃላፊነት አንወስድም። በዚህ ሳይት ላይ ያሉት መረጃዎች ለአጠቃላይ ዕውቀት ብቻ የቀረቡ ናቸው፤ ሌሎች ቀዳሚ፣ ይበልጥ ትክክለኛነት ያላቸው፣ ይበልጥ የተሟሉ፣ ወይም ይበልጥ ወቅታዊ የሆኑ የመረጃ ምንጮችን (የቤተሰብ ሐኪምዎን አካትቶ) ሳያማክሩ ውሳኔ ለመወሰን የቀረቡ አይደሉም። በዚህ ሳይት ላይ ባለው መረጃ ላይ በምንም መልኩ ቢመረኮዙ በራስዎ ኃላፊነት ነው።

ግላዊ መረጃ

ግላዊ መረጃዎ የሚተዳደረው በግላዊነት ፖሊሲያችን ነው።

ይዘት (ኮንቴንት) እና ፈቃድ (ላይሰንስ)

ዲፒኤስ የተወሰነ፣ የብቻዎ ያልሆነ፣ ግላዊ፣ ማስተላለፍ የማይቻል፣ ለሌላ አካል ማጋራት የማይችሉት፣ እና ሊነጠቁት የሚችሉት መብት እና ፈቃድ (ሀ) ሳይቱን እዚህ ላይ ለተቀመጠው ዓላማ በእነዚህ መመሪያዎች መሠረት ለመክፈት፤ እና (ለ) በሳይቱ የቀረቡ ማንኛቸውም መረጃዎችን እና መዝገቦችን (ዶኩመንቴሽኖችን) ለግልዎ፣ ለንግድ ላልሆነ እና ለመረጃነት ጥቅም ብቻ ለመክፈት፣ ለማየት እና ፕሪንት ለማድረግ። ዲፒኤስ በማንኛውም ሰዓት እና በማንኛውም ምክንያት ይህን ፈቃድ ሊያቋርጠው እና እርስዎ ሳይቱን እንዳይከፍቱ ሊያግድ ይችላል። እዚህ ጋር በግልጽ ያልተቀመጡ መብቶች በሙሉ ለዲፒኤስ ብቻ የተጠበቁ ናቸው።

በሳይቱ አማካይነት የሚቀርቡ ማንኛቸውም አይነት ይዘቶች (ኮንቴንቶች) እና ዳታዎች በሙሉ (የ”ዲፒኤስ ኮንቴንት”) ባለቤትነታቸው በብቸኝነት እና ያለ ተጋሪ የዲፒኤስ እና/ወይም የሦስተኛ ወገኖች ነው። እርስዎ ሳይቱንም ሆነ ማንኛውንም የዲፒኤስ ኮንቴንት ማስተዋወቅ (ማርኬት ማድረግ)፣ መሸጥ፣ ገዝቶ መሸጥ፣ ወይም ለንግድ መጠቀም አይችሉም። ማንኛቸውም አይነት አስተያየቶችን፣ ጥቆማዎችን፣ ምክሮችን፣ ወይም መጠይቆችን ወይም ሌላ ማንኛውም አይነት አስተያየት (“አስተያየት”) እርስዎ ለዲፒኤስ ካቀረቡ ዲፒኤስ ይህን አስተያየት ሳይቱን ለሌላ ለማንኛውም ዓላማ ለማሻሻል ሊጠቀምበት ይችላል። በተጨማሪም ዲፒኤስ የእነዚህ አስተያየቶች ባለቤትነት ይኖረዋል፤ እናም ዲፒኤስ እና አጋሮቹ፣ ፈቃድ የሰጣቸው አካሎች፣ ተጠቃሚዎቹ፣ ሽርኮቹ፣ ሦስተኛ ወገን አቅራቢዎቹ እና ሌሎች የተፈቀደላቸው አካላት አስተያየቶቹን ሊጠቀሙ፣ ፈቃድ ሊሰጡ፣ ሊያከፋፍሉ፣ ሊያባዙ፣ እና ለንግድ ሊያውሉ ይችላሉ፣ እርስዎም ማንኛቸውንም መሰል አስተያየቶችን በማይቀለበስ፣ ተጋሪ በሌለው እና ተቆራጭ ለእርስዎ በማይታሰብልዎ ሁኔታ ለዲፒኤስ እንግዲህ ሰጡ።

ሁሉም የምርት፣ የብራንድ እና የዲፒኤስ ስሞች እና ሎጎዎች፣ እንዲሁም በሳይቱ ላይ የሚገኙ ወይም ከሳይቱ ጋር በመያያዝ ጥቅም ላይ የሚውሉ የንግድ ምልክቶች በሙሉ የዲፒኤስ (ወይም የአቅራቢዎቹ፣ የሽርክ ቢዝነሶች ወይም የሦስተኛ ወገን ፈቃድ ወሳጆች) የንግድ ምልክቶች ናቸው። ያለ ዲፒኤስ ወይም እንደ ተገቢነቱ የምልክቱ ባለቤት የጽሑፍ ፈቃድ በሳይቱ ላይ የሚታዩም ሆነ ተያይዘው የሚመጡ ማንኛቸውንም የንግድ ምልክቶች ማንኛውም ጥቅም ላይ ማዋል ፈጽሞ የተከለከለ ነው።

የተከለከሉ አጠቃቀሞች

በእነዚህ መመሪያዎች ከተቀመጡት ክልከላዎች በተጨማሪ ሳይቱን ለሚከተሉት ዓላማዎች ከመጠቀም እርስዎ ተከልክለዋል፦ (ሀ) ለማንኛውም ሕገወጥ ዓላማ፤ (ለ) ሌሎች ሰዎችን ማንኛቸውንም አይነት ሕገወጥ ድርጊቶች እንዲያደርጉ ወይም እንዲሳተፉ ለመጠየቅ፤ (ሐ) ማንኛቸውንም ዓለም አቀፋዊ፣ ፌደራላዊ፣ የፕሮቪንስ፣ ወይም የስቴት መመሪያዎችን፣ ደንቦችን፣ ሕጎችን፣ ወይም አካባቢያዊ (ሎካል) ሥርዓቶችን ለመጣስ፤ (መ) የእኛን የአእምሮ ንብረት መብቶችን ወይም የሌሎችን የአእምሮ ንብረት መብቶችን ለመጣስ፤ (ሠ) ጾታ፣ ወሲባዊ ምርጫ፣ ኃይማኖት፣ ብሔር፣ ዘር፣ ዕድሜ፣ ትውልድ አገር፣ ወይም ስንኩልነት ላይ ተመሥርቶ ለመተንኮስ፣ ለመበደል፣ ለመስደብ፣ ለመጉዳት፣ ስም ለማጥፋት፣ ለማንቋሸሽ፣ ለማቃለል፣ ለማስፈራራት፣ ወይም ለማዳላት፤ (ረ) ሐሰተኛ ወይም አሳሳች መረጃን ለመስጠት፤ (ሰ) የሳይቱን ወይም ሌላ ግንኙነት ያለውን ዌብሳይት ወይም ሌሎች ዌብሳይቶች ወይም የኢንተርኔቱን አሠራር (ፈንክሽናሊቲ) እና ኦፕሬሽን የሚያበላሽ ወይም ወይም ሊያበላሽ በሚችል በማንኛውም አይነት መንገድ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ቫይረስ ወይም ሌላ ማንኛውም አይነት ጎጂ ኮድ አፕሎድ ለማድረግ ወይም ለማስተላለፍ፤ (ሸ) የሌሎችን ግላዊ መረጃ ለመሰብሰብ ወይም ለመከታተል፤ (ቀ) ስፓም፣ ፊሽ፣ ፋርም፣ ፕሪቴክስት፣ ስፓይደር፣ ክሮውል፣ ወይም ስክሬፕ ለማድረግ፤ (በ) ለማንኛውም የብልግና ወይም ኢሞራላዊ ዓላማ፤ ወይም (ተ) የዌብሳይቱን ወይም ማንኛውም ተዛማጅ ዌብሳይትን፣ የሌሎች ዌብሳይቶችን፣ ወይም የኢንተርኔቱን የደኅንነት ፊቸሮች ለመረበሽ ወይም ለማለፍ። ከተከለከሉት ዓላማዎች ውስጥ ማንኛቸውንም በመፈጸምዎ ምክንያት ዌብሳይቱን ወይም ማንኛውንም ተዛማጅ ዌብሳይት ከመጠቀም እርስዎን የማገድ መብታችን የተጠበቀ ነው።

ማስተባበያዎች እና ካሣ

ሳይቶቹ በዲፒኤስ “እንደ ሆነ” እና “እንደ አለ” የቀረቡ ናቸው። ዲፒኤስ የዲፒኤስ ኮንቴንቶችን እና የሳይቱን ፈንክሽናሊቲ በማንኛውም ጊዜ ለእርስዎ ቅድመ ማሳወቂያ ሳይሰጥ ለውጥ ሊያደርግ እና ሊያሻሽል ይችላል። ዲፒኤስ ሳይቱ ወይም ዲፒኤስ ኮንቴንት በማንኛውም ጊዜ ወይም ቦታ ስለ መገኘቱ ወይም ሳይቱ ከማንኛቸውም አይነት ቫይረሶች ወይም ሌሎች ጎጂ አካላት ነፃ ስለመሆኑ ዋስትና አይሰጥም። ዲፒኤስ ስለ ሳይቱ ቴክኒካዊ ትክክለኛነት ወይም ፈንክሽናሊቲ ወይም የዲፒኤስ ኮንቴንቱ ትክክልኛ፣ ስሕተት አልባ እና የዘመነ ስለመሆኑ ምንም ውክልና አያደርግም። ዲፒኤስ ምንም ውክልናዎችን አያደርግም ዋስትናዎችን ወይም ማንኛቸውም አይነት ሁኔታዎችን፣ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የተጠቀሱ፣ የሚከተሉትን የሚያካትቱ ግን በሚከተሉት የማይወሰኑ፦ ለአንድ ዓላማ፣ ርዕስ፣ ወይም የሦስተኛ አካል መብቶችን ወይም አእምሮ ንብረቶችን ላለመጣስ ተገቢነት።

በማንኛውም ክስተት ዲፒኤስ፣ ዳይሬክተሮቹ፣ ጽሕፈት ቤቶቹ፣ ተቀጣሪዎቹ፣ ኤጀንቶቹ ወይም ተወካዮቹ ለሚከተሉት ለማንኛቸውም ተጠያቂ አይደሉም፦ ማንኛውም አየነት ቀጥተኛ፣ ቀጥተኛ ያልሆነ፣ ክስተታዊ፣ ልዩ፣ ቅጣታዊ ወይም መዘዛዊ የሚከተሉትን የሚያካትቱ ነገር ግን በሚከተሉት የማይወሰኑ ውድመቶች፦ ከግለሰብ ጉዳት ወይም የዳታ መጥፋት፣ ዲፒኤስ ጥፋቶቹ ሊደርሱ እንደሚችሉ ተመክሮ ቢሆንም ባይሆንም፣ በማንኛውም የተጠያቂነት ጽንሠ ሐሳብ፣ ሳይቱን በመክፈት፣ በመጠቀም ወይም በሳይቱ ፐርፎርማንስ ወይም ማንኛውም ኮንቴንት ወይም ሌላ መረጃ ከሳይቱ ጋር ተያይዞ እስከቀረበ ድረስ፣ ወይም ከእነዚህ ጋር ተያይዞ። እነዚህ ወሰኖች ተገቢ የሚሆኑት ማንኛውም የማንኛውም የተወሰነ መፍትሔ የመሠረታዊ ዓላማ ብልሽት በስተቀር ይሆናል።

ዲፒኤስን፣ ባለቤታችንን፣ ንዑስ ድርጅቶቻችንን፣ አጋሮቻችንን፣ ሽርኮቻችንን፣ መኮንኖቻችንን፣ ዳይሬክተሮቻችንን፣ ኤጀንቶቻችንን፣ ኮንትራክተሮቻችንን፣ ፈቃድ ወሳጆቻችንን፣ አገልግሎት አቅራቢዎቻችንን፣ ሰብኮንትራክተሮቻችንን፣ አቅራቢዎቻችንን፣ ኢንተርኖቻችንን፣ እና ተቀጣሪዎቻችንን ከማንኛውም ይገባኛል ወይም ጥያቄ (እርስዎ እነዚህን መመሪያዎች ወይም በሬፈረንስ የሚያካትቷቸውን ዶክመንቶች በመጣስዎ ወይም ማንኛውንም ሕግ ወይም የሦስተኛ ወገን መብት በመጣስዎ ምክንያት ወይም በእነዚህ መዘዝ በማንኛውም ሦስተኛ ወገን የሚመከፈሉ ምክንያታዊ የጠበቆች ክፍያዎችን ያካትታል) ለመካሥ፣ ለመከላከል እና በጉዳት አልባነት ለመያዝ እርስዎ ተስማምተዋል።

የሦስተኛ ወገን ሳይቶች

በሳይቱ ላይ ያሉ ማንኛቸውም ወደ ሦስተኛ ወገን ዌብሳይቶች የሚወስዱ ሊንኮች የሚቀርቡት ለእርስዎ ሥራ ለማቅለል ነው። ሦስተኛ ወገን ዌብሳይቶችን ለመክፈት ወይም ከሦስተኛ ወገኖች ምርቶችን ወይም አገልግሎቶችን ለማግኘት ከመረጡ እነዚህን የሚያደርጉን ሙሉ በሙሉ ኃላፊነቱን በራስዎ በመውሰድ ይሆናል፣ ይህ ድርጊትዎም በእርስዎ እና በሦስተኛው ወገን መሀል የሚደረግ ነው። ዲፒኤስ በእነዚህን መሰል ዌብሳይቶች የሚቀርቡ ኮንቴንቶችን ሕጋዊነት፣ ሐቀኝነት ወይም ትክክለኛነት፣ ወይም በሦስተኛ ወገኖች የሚገርቡ ማንኛቸውንም ምርቶች እና አገልግሎቶች በተመለከተ ዋስትና አይሰጥም፣ ምንም አይነት ውክልናም አያደርግም፣ እነዚህን ዌብሳይቶች፣ ምርቶች እና አገልግሎቶች በመጠቀም ለሚመጣ ማንኛውም አይነት ጥፋት ወይም ጉዳት ተጠያቂ አይሆንም። እነዚህን ውጫዊ ዌብሳይቶች እና ሪሶርሶች ከመጠቀምዎ በፊት የአገልግሎት መመሪያዎቻቸውን እና ግላዊነት ፖሊሲያቸውን እንዲመለከቱ አበክረን እንመክርዎታለን። በማንኛውም ጊዜ ለማንኛውም ምክንያት ዲፒኤስ ወደ ውጫዊ ዌብሳይት ወይም ሪሶርስ የሚወስድ ሊንክን ሊያጠፋ እንደሚችል እርስዎ ዕውቅና ይሰጣሉ።

ገዢ ሕግ

እነዚህ መመሪያዎች እና እዚህ ሪፈረንስ የተደረጉ ማንኛቸውም ዶክመንቶች እዚህ ላይ ተፈጻሚነት በሚኖራቸው በኦንታሪዮ ፕሮቪንስ ሕጎች እና በካናዳ ፌደራል ሕጎች የሚገዙ እና የሚወሰኑ ይሆናል። በዚህ ለሚነሱ ሁሉም ጉዳዮች እና ጥሎች በብቸኝነት ሥልጣን የሚኖራቸው የኦንታሪዮ ፕሮቪንስ ፍርድ ቤቶች እንደሆኑ እርስዎ ስምምነትዎን ይሰጣሉ።

መላው ስምምነት

እነዚህ መመሪያዎች እና የግላዊነት ፖሊሲው በእርስዎ እና በዲፒኤስ መካከል የሚደረገውን ስምምነት በአጠቃላይ ይይዛሉ። ይህም የሚያያዘው ሳይቱን ከመክፈት እና ከመጠቀም ጋር ነው፣ ከሌሎች ከዚህ ጊዜ በፊት የወጡ ወይም በአሁኑ ጊዜ ካሉ በእርስዎ እና በዲፒኤስ መሀል በቃል ወይም በጽሑፍ ከሚኖሩ ስምምነቶች፣ ድርድሮች፣ እና ፕሮፖዛሎችም በላይ ገዢነት ይኖራቸዋል። በእነዚህ መመሪያዎች ውስጥ የተደረጉት ሁሉም ኪዳኖች፣ ስምምነቶች፣ ውክልናዎች፣ እና ዋስትናዎች የእርስዎን እነዚህን መመሪያዎች መቀበል እና የእኛ እና የእርስዎ ግንኙነት መቋረጥን አሳልፈው ይኖራሉ። እርስዎ እና ዲፒኤስ እነዚህ ተርሞች እና ከእዚህ ጋር የሚዛመዱ ዶክመንቶች በእንግሊዝኛ እንዲጻፉ ትስማማላችሁ። Nous avons demandé que cette convention ainsi que tous les documents qui s’y rattachent soient rédigés en Anglais.

ስለ ተቋራጭነት እና ስለ መተው (ዌይቨር)

ከእነዚህ መመሪያዎች ማንኛቸውም ተገቢ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት አማካይነት የማያገለግል ወይም በምንም መልኩ ተፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል ቢወሰን ከማያገለግሉት እና ተፈጻሚ ሊሆኑ ከማይችሉት ነጥቦች በቀር ሌሎቹ የእነዚህ መመሪያዎች ነጥቦች ወይም እነዚህ መመሪያዎች በሰዎች ወይም ሁኔታዎች ላይ የሚኖራቸው ተፈጻሚነት በእዚህ ተጽዕኖ አይመጣበትም፣ እነዚህ ነጥቦች እያንዳንዳቸውም ሕግ እስከሚፈቅደው መጠን የሚያገለግሉ እና ተፈጻሚነት የሚኖራቸው ይሆናሉ። በእነዚህ መመሪያዎች የተሰጡንን መብቶች ወይም ሥልጣኖች ማንኛቸውንም ለማስፈጸም ብንዘገይ ወይም ባናስፈጽም፣ ወይም የእርስዎ በጊዜ እና ሙሉ በሙሉ ኪዳንን ለመፈጸም አለመቻልን ለመቃወም ብንዘገይ ወይም ባንቃወም፣ እነዚህን ማድረጋችን በምንም መልኩ እነዚህን መብቶች እና ሥልጣኖች ከእኛ ሊወስድ ወይም በቀጣይ ጊዜያት የሚመጡ ጥሰቶችን ወይም ማንኛውም ሌላ ኪዳንን እንደተውን (ዌይቭ እንዳደረግን) ሊያመላክቱ አይችሉም። ዲፒኤስ ማንኛውም መተዎች (ዌይቨሮች) ቢያደርግ መሆን ያለበት በጽሑፍ እና ሥልጣኑ ያለው የዲፒኤስ ተወካይ ፈርሞበት ነው።

መመደብ

እነዚህ መመሪያዎች ለእርስዎ ለግልዎ ናቸው፣ እርስዎ ዲፒኤስ አስቀድሞ በጽሑፍ ሳይፈቅድ ለሌላ ሰው መመደብ፣ ማዘዋወር፣ ወይም ማጋራት አይችሉም። ዲፒኤስ ያለ የእርስዎ ፈቃድ እዚህ ካሉት መብቶቹ እና ግዴታዎቹ የትኛዎቹንም ሊመድብ፣ ሊያዘዋውር፣ ወይም ሊወክል ይችላል።

ኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶች

ይህ ኤሌክትሮኒክ ዶክመንት እና እዚህ ሪፈር የተደረጉ ወይም የተካተቱ ሁሉም ሌሎች ኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶች የሚከተሉትን ይሆናሉ፦ (ሀ) ለሁሉም ዓላማዎች እንደ “ጽሑፍ” ወይም “በጽሑፍ” ያሉ እንደሆኑ ይቆጠራሉ እና ከሁሉምም ከጽሑፍ ለሚጠበቁ የድንጋጌ፣ የኮንትራክት፣ እና ሌሎች የሕግ መስፈርቶች ይስማማሉ፤ እና (ለ) እንደ የተፈረመበት ስምምነት ሆነው በሕግ ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል።

የማግኛ መረጃ

ስለ እነዚህ መመሪያዎች ጥያቄዎች ወይም አስተያየቶች ካለዎ እባክዎ privacy@digitalpublicsquare.org ላይ እኛን ኮንታክት ያድርጉን።